አንች ሆየ ስልሸ ደስታ ይሰማኛል
ቅዳሴ ቁሜያለዉ ለዉበትሽ ፀዳል
ለመልክ ለቁመናሽ አቤቱ ይባላል
ዳኝነት ይቆማል ችሎት ይሰየማል
ለቁንጅናሽ ህብረት ፊደል ይመረጣል
እንደኔ ገጣሚ ስላንች ይቀኛለል
ፍሪዳ ይጣላል ቁርጥ ስጋ ይበላል
በዉበትሽ ምክንያት በዉበትሽ ሀይል
ደሀና ሀብታሙ ባንድ ጣራ ስር እኩል ዉሎ ያድራል
እናም አንች ሆየ ስልሸ ደስታ ይሰማኛል
በልቤ መንበር ላይ በህቡ ነግሰሻል
አንች ሆየ ስልሸ ፍሰሀ ይሆናል
አንች ሆየ ስልሸ ጥሩ አየር ይነፍሳል
ኢትዮጵያየ ዉዴ ... የሀገር ቅምጥል
የአንች ሆየ ሀሴት የትዉልድ ሀመልማል
አንች ነሽ የግሌ ሱስ የራሴ አመል
///////////////////////
27/6/12
No comments:
Post a Comment