መይሳዊያን (ቁጥር 2 የግጥም መድብል)

መይሳዊያን


 ....... 40 ግጥሞች .......

 በአንድነት ደምሴ (አንዱ መላ)  
            ....     
            

                  
ምስጋና 

መይሳዊያን የተሰኘችዉ ይች የግጥም መድብሌ

  
ለምወዳት እናቴ ለፍቅሬ ጋርደዉ
  
ለወድሞቸ ፡  

ለክቡር ደምሴ
ለታደለ ደምሴ
ለኤፍሬም ደምሴ ፤   

ለአሳዳጊ አባቴ ለደምሴ መላኩ

ለአክስቴ ለእስከዳር ጋርደዉ 

ለዘመዴ ለኮማንደር መሰረት ደባልቄ
  
  
ለጥበብ ጉደኞቸና ለመይሳዊያን በሙሉ
  
እንዲሁም ለመቅደላዉ ጀግና ለአጼ ቴዎድሮስ
የፍቅር መታሰቢያ ትሁንልኝ ፡፡ 

................... 
 
 ቁጥር 0  መግቢያ (መቅድምቅኔ


የጣቶቸ ሁለት ቀለበቶች

የቅኔ ግጥም ድግምቶች

የህይወቴ  ሚስጥራዊ  "አባባሎች"

............   

መይሳዊያን ይሉናል በስም የሚያቁነ
 
እኛ ከሰለጠን ቆየን ከነቃነ
 
አምልኮ መይሳዉ ዋና ስራችን ነዉ
 
ሹርባ በመሰራት ንጉሱን መስልነዉ
 
ጫት በመቃም ተግባር በምርቃና አወቅነዉ
 
በግጥም በስንኝ መዩን አደነቅነዉ ቴዲን አመለክነዉ 

.........  


Dedicated to Gonder, Debretabor, Gayent heroes of this Generation and for all brave Ethiopians.

(ማስታዎሻነቱ ለዚህ ትዉልድ ለጎንደር ፤ ለደብረታቦርና ለጋይንት ጀግኖች፤ እንዲሁም ለሁሉም ጀግና ኢትዮጵያዊያን ሁሉ ይሁን ፤፤)
 

 ///////////////// 

 

  1

የንጋት ኮከብ  

ብሄራዊ አዲስ አበባ በፈርማታዉ ተራ

ያየዉህ ኮከብ ሰዉ በጻፍከዉ ፈጠራ

በእጆችህ እንቁዎች በኪነት አዝመራ
 
በዉሴጤ የእዉቀት ዘር እሸቱ አፈራ 
 
 የጓዳናዉ ኑዋሪ ባይታዋሩ ጀግና
 
 አዲስ እኔነቴ አንተን በማየቴ በልቤ ላይ ጸና 

 አሁን አስባለዉ እዉቀትን ሳጠና 
 
 ቀይሳህልና አዲስ የህይወት ፋና 

በዘመኔ ሁሉ እንደንጋት ኮከብ ታበራለህ ገና 
 
      ......///.....
      25/7/10 
 
   2

ምን ተስኖህ ላንተ  

በለተ ፋሲካ በቀራኒዎ ድል
 
በትንሳኤዉ ማግስት በመገለጥ ክልል
 
ቶማስ ሲጠራጠር እጅህን ልይ ሲል
 
መቅደላዊት ማርያም በደስታ ስትማልል
 
በመገለጥ ሞግስ የሀዋርያት ሀሴት
 
ሞትን ድል የነሳህ አንተ ቃል ህይወት
 
ምን ተስኖህ ላንተ ድንቅ ተአምር ለመስራት
 
አዳምን ያረሳህ ተስፋዉን የጠበቅህ 
 
በስጋዌ ወደሙ በድህነት ያጸናህ
 
ቁስላችን ላንዴ ለዘላላም  የፈወስክ በደምህ
 
ምን ተስኖህ ላንተ ከሆነ ፍቃድህ   

          .......///.....
          27/7/10 
 
    3
 
እንደ ህላዌ መልህቅ    


የተነበርሽ ዉቢት አንችን ያልኩኝ እለት
 
የትነበርሽ የኔይቱ በዚያች ያንች ቅጽበት
 
ፍቅርሽ ተሰዉሮ በግርዶሽ ሲያጠላ
 
አልፋታኝ ብሎ በብዙ መሀላ
 
አንችን ማለት ሀጢያት መርገምን እንዲያክል
 
ስምሽን ባለማሰብ ዉስጤ እንዳይታለል
 
ከብዙ ልምምዱ ድፍረቱን አግንቸ

አንችን በማሰቤ እኔን እረስቸ
 
በዚህ ሁሉ ነገር ፍቅሬን እገልጸዉ ዘንድ
 
በሚያምር ግጥም በብዙ መዉደድ 

የቃል ምርጫየ ይፍሰስ ይጎድጎድ 

ፍቅሬ ይፈንዳ ይግባ ስር ይስደድ 

እንደህላዌ መልህቅ እንደለየለት እብድ 

እዎድሻለዉ የእኔ ዉድ
 
   .........///............
   5/10/09  

 4
 
የማያየዉ ዉበት 
 
    
አንችን ማየት ደጉ አንችን ማየት ልማድ

በማስተዋል ጉዞ በማስተዋል መንገድ 

አጥብቄ ስመኝሽ አንችን ከልብ ስወድ 

በየዉሽ ቅጽበት ምት አይኖቸ ሲጓጉ 
 
አይኖቸ አይኖችሽን ሊያዩ ሲፋልጉ
 
እኔን ባለማየት በሴትነትሽ ወግ 

አታይኝም ነበር ባማያይ ዉበት ህግ 

አንዴ እንኳ አይዳለም ሳታይኝ ያለፍሽዉ
 
ለወደደ ልቤ ትኩረት የነፈግሽዉ 

 ደጋግመሽ አታይኝ ዉዴ ምን አጠፋዉ 

ያን መልካም ዉበትሽን ሴትነትሽ ዋጠዉ 

 ዘምበል ደፋ ስትይ በዚያ አረማመድ
 
 በዚያ አንች እረምጃ በዚያ የአንች አካሄድ 

እኔም በበኩሌ አንችኑ በማየት ተመስጦየ ሲያድግ 

እኔን አለማየት ለአንች ሆነሽ ማረግ
 
           ......///....
          28/7/10

 5
 
አይደል እንዴ
  
መልክአ_ጸዋ ድግምት ምትሀት 
  
አይደል  እንዴ የቀደም ፈዉስ ድህነት 

የጥንት እዉነት ጥበብ እዉቀት 

አይደል እንዴ በስማ ብሎ መድገም
 
በማልዳ ድባብ ደብር መሳም 

የድህነት ሁሉ ቃል  ቅድስ ስም
 
ከእብደት የሚሰዉር የሚፈዉስ ከህመም
 
 አይደል እንዴ መልክአ ስርየት
 
ድግምት ክኒን ነገር የህይወት
 
ከለላየ ያመለጥኩበት ከሞት
 
የአባቶቸ ስጦታ የአባቶቸ ጥሪት 

ደጋግሞ ስምን መጥራት አቤት ማለት
 
አይደል እንዴ ክቡር አስማት
 
   //////////
27/9/10  
 
6
 
በህይወቴ መዋል
 
ከዘሪዉ ክርስቶስ መዋል
 
 ከዚያች አንዲት አመልማል
 
 ሰባኪዉ ለሰዎች ሲያድል
 
የደረሰችኝ አንድ እዉነት ናት
 
 የህይወቴ መዋል የምላት
 
 ዘሪዉ በአጸናፍ ሲናገር 

በተራራዉ ጫፍ  ስብከት ሲጀመር
 
 ተሰዉሮ የሚቀር ነገር የለም ይል ነበር
 
አንዳች ህብር ወዘለምስጢር ገሀድ ይወጣል 
  
 በእልፍኝ የተነገር  በሰገነት ይሰበካል
 
 በጨለማ የተሰራ በብርሃን ይገለጣል 

 ይላል ክርስቶስ ሲያድስ
 
 በቅዱስ ቃሉ እኔንም ሲያደርስ
 
እናም በህይወቴ መዋል
 
ምንም ነገር ቢያብል
 
ምንም ነገር ቢያክል
 
ቀን ጠብቆ ይገለጣል
 
 ስኬት በስዉር ስራ ይጸድቃል
 
ጥበብ በዚህም ታይቷል
  
       //////////////
         25/9/10 
 
      7

ዉቢት ካሉሽ አይቀር 

 
ዉበት ጸሀር አለዉ የተጣለለ ዶፍ
 
 ማየት የፈለገ አይኑ ካንች ላይ ሲያርፍ
 
 የፍቅር ምታትሽ ሲታወጅ ወይ ሲጻፍ
 
 በዚህ መካከል ላይ አይን የወጋዉ ስለት
 
የሰዉ ፊት ያረፈዉ ያች ትንሽ ቅጽበት
 
መአት ታመጣለች መከራ ህማማት
 
 ስለዚህ ለዉበትሽ ልክ መጠን አብጅለት 

ዉቢት ካሉሽ አይቀር እንከን የሌለበት
 
ከመኳኳሉ ጋር ጸሎት ጨምሪበት
 
ያች ቀጭን እዉነት የምትወስድ ወደ ሞት
 
 ዉበትሽን ሳትገላት ቀድመሸ ድረሽባት
 
      ///////////////
        25/9/10 
 
    8
 
ካልመሽ አይነጋም
 
 
ለካስ ከእኔ ጋር ፈንታሽ ተቆራኝቷል
 
በሀዘን በደስታሽ ውስጤም አብሮሽ ደምቷል
 
በነገር ጠባሳ ባይበሉብሽ ጥፊ
 
ፍቅር ይበረታል ተሎ አታኩፊ
 
ትንሽ ካለተመታ ዉበትሽ በበትር
 
 መኖርሽ ከእኔጋ በምን ይመስጠር
 
ከአንች ጋር ማደሬስ በምን ይጠረጠር
 
የመኖርሽ ምስጢር በምን ቃል ይነገር
 
ስለዚህ ዉዴ ሆይ ትንሿ ሀዘንሽ
 
 እኔን ያዛዘነኝ ጠባሳዉ  የልብሽ  
 
ሀዘን እና ደስታ ያፈራረቅብሽ
 
የደስታሽ ምንጭ ናታ  ከላይ የተስጠሽ
 
 እንደአልጋዋ ትግል ምስጢር የመኖርሽ
 
 ካልመሽ አይነጋም በእኔ ይሁንብሽ 

 ቀን ይገፋል እንጅ እራብ ነዉ እሚያጠግብሽ
 
             ___///____
              14/9/10
 
    9

የአይን ማረፊያ የአይን ቀለብ 
 
 
አይደለሽ እንዴ ዉብ መልከ ሸጋ
 
መሀበሉ ሁሉ በአንች ጥላ የሚረጋ
 
ጎበዝ ወጣቱ ከረምጃሽ ጋር የሚተጋ 
 
 አይደለሽ እንዴ አንች ኮረዳ
 
 እንደተጠመደ ቦምብ ቀን ጠብቆ እንደሚፈነዳ
 
ዳሌሽ ከወገብሽ በታች ፍንቅሎ ሊዎጣ የሚዳዳ
 
አንች የአይን ማረፊያ የአይን ቀለብ
 
እስኪ በፍቅር ሀይል እንሳሳብ
 
እስኪ በፍቅራችን ሙዳይ እንዋብ
 
እንደ እንቦሳ ጥጃ ፈንጥዘን ካልጨረስን
 
መች የልባችን አወራን እስኪበቃን ተቀራርበን 

መች አይን ለአይን ተያየን
 
አዳንችን ለአንዳችን  መች ተረፍን
 
በይ እስኪ የአይኔ ማረፊያየ የአይኔ ቀለብ 
 
ቀይ ዶሮየ የኑሮ መላ አኗኗሬ ደንብ
 
 እስኪ በቃን ድረስ እንቀራረብ 
 
         //////// 
       9/9/10 
 
      10
 
ቁንጅናሽ መብቃቱ 

 
ትናንት  እታዛዉ ስር እረግረጉ ቦታ
 
የፍቅርሽ ህላዌ ትዝታሽ በረታ 

አሮንቃዉ ይዞኛል አላራምድ ብሎ
 
መዉደድሽ በፈንታዉ ሽክምን አክሎ
 
እግረሽ ስር ላይ ጣለኝ እላይ አከባሎ
 
አንች የሴት ቁንጮ የሴቶች ወይዘሮ
 
ይገባሽ የለም ወይ የወንድ አዉራደሮ
 
ይጠብቅሽ የለ ጀግና በአመክሮ
 
አምሳያሽ ይታያል በመስክ በተፈጥሮ
 
ስለዚህ ሙናየ ባሮቃዉ በጓዳዉ
 
የሚነገርልሽ ወሬ የሚሰማዉ
 
ቁንጅናሽ መብቃቱ ነዉ ሚታወቀዉ 
 
         /////////////////
             28/9/10
 
   11
 
የፒያሳ ቁንጅና
              
        
ሲያስጮህ ያደረ የፒያሳን ቁንጅና

በልደት ቀን ተስፋ በልደት ናሙና

በጠሀይቱ ሰፈር በፒያሳ ገመና

 በጎንደር በሽገር በስዎች ህሊና

በአንዲት ሌሊት አዳር

በሽርሙጣ ወሬ በሴትነት ምክር

ወንድነት ሲፈተሽ ወንድነት ሲዘከር

ድምጾን ያስማችዉ ይበቃል እያለች

ያንተን ወንድነትክን እሷ መስክራለች

ለአጥቢያዉ ለአልቤርጎዉ አሳይተሀለች

እሷ መሰክራለች__

እንቅርት እንዳለህም ሄዋን ሁነሀለች

 ልጅቷን አትርሳ ሰላም ሰተሀለች
         //////////////////        
            1/10/10

   
  12

 ሰለሞን ወግሩም 
 
ዉድ ናችዉ ለእኔ የፍቅር እማማት

የመሳሳብ ዉጤት የወድነት ስሜት

 በጥበብ አለም ላይ በጥበብ ጎጆ ቤት

 ያወኳችሁ ሰዎች ሁለት ክዋክብት

 ሰለሞን ሳህለ ወግሩም ኤርምያስ

ፍትወተ ስጋ የልብን የሚያደርስ

የለም ከዚህ በለይ በቃል የሚሞገስ

እናንተ ጓዶቸ የጥበብ ሀብቶቸ

ይሀዉ ወደድኳችዉ ከመንጋዉ ለይቸ

 ዉብና ወንዳወንድ ናችዉ ጓደኞቸ

 ስለሞን ገጣሚዉ ግሩም ተዋናዩ

ዉስጤ ባለቦታ በመንበር ተለዩ

የፍቅራችን  ወጎች ጎልተዉ እዲታዩ
        /////////////
           8/9/10     
   
 13 

አማራ ነኝ ነፍጠኛ 

 
የትም ፈልገኝ ታገኘኛለህ
 
 በነፍጤ ስለት ትለየኛለህ
 
 አፈር ገፊ ነኝ የገበሬ ልጅ
 
  ከአፈር ወስጅ ሰዉን የማበጅ
 
  በጎንደር ጎጃም በወሎ አዋጅ
 
  ነቅሎ የወጣ ከሳት የሚፋጅ
 
 ደም ያለኝ ትኩስ አማራ ፍላት
 
 ተወግቶ ማደር የማይሆንለት
 
 አልሽነፍ ባይ አንዳች መለከት
 
 አማራ ነኝ ጓድ ፋኖ ነፍጠኛ
 
 ለጠላቴ እንደዉ ለአፍታም አልተኛ
 
 በስሜ  ጥራኝ  ተቀበለኛ
 
 የአራዳዉ ጉራ  አንተ ወርኛ
 
 ወንድነት ካለህ ግጠመኛ
 
 በስሜም ጥራኝ ብለህ ነፍጠኛ
 
  ///////////////////////
         2/10/10 

   14

 
የከንፈርሽ ጸጋ 

 
ትናንሽ ከንፈሮች የአንች ባይሆኑም

ለእኔ እንደተሰጡ ሀገሬዉ ባያዉቅም

አንችን በመሳሜ መዳኔን አልክድም

ባልሳም አረባም ባልሳም አልሰራም

ትንፋሽሽ ባይሞቀኝ ሽታሽ ባያሳሳኝ

አንዳች የእኔ የምለዉ ሰዉነት ባልኖረኝ

ያም ሁኖ ከናፍሮችሽን አጥብቄ እሻለዉ

ከመላ አካልሽ እነሱን ለመሳም እጅግ እወዳለዉ

የከናፍሮችሽ የተፈጥሮ ጸጋ

እንደጸጌረዳ እንደምተዋጋ

ጠዉልጋ እንደማታዉቅ በክረምት በበጋ

እንደምትጠበቅ መሽቶ እስከሚነጋ

ወይም እንደዉብ አበባ እንደምትፈነድቅ

እንደዉድ የአንገት ጌጥ ከአንገት እንደማይወልቅ

እንደንጉስ እልፍኝ በሽ እንደሚጠበቅ 

ከናፍሮችሽን እየሳምኩኝ ላድንቅ  
   /////////////////
      3/10/10

   15
 
         ኋላሽን ስወደዉ
 
 እልፍ ባልሽ ቁጥር ኋላሽን አያለዉ
 
መቀመጫሽ ዉቡ አንዳች መስብ አለዉ 

የአካሄድሽን ቅንጦት ቅርጹን አዉቀዋለዉ
 
ቀጥቀጥ ባለ ጊዜ መቀመጫሽ ከታች
 
አቤት ምቱ ሲያምር አቤት ቅርጹ ሲመች
 
 አንች ማየት ማቆም አይኖቸን ለመንቀል 
 
ተሰኖኛል እኔ ወድጅም እኳ አይደል
 
  ወፍራም ኋላሽን የመቀመጫሽ ሀያል
 
 በምን ነዉ እሚወከል በምንስ ይመሰል
 
 የዳሌ ትባብቅሽ የባትሽስ ነገር
 
እር ምን ተነገሮ የኋላሽ ፍቅር
 
በተለይ ግን ያን ቅርጸ መቀመጫሽ ድብር
 
አልጠግበዉም እኮ ሳስበዉም ባድር
 
መቀመጫሽ ደጉ በቅጡ ቢስፈር
 
ቢነገር ዉበቱ ኋላሽን ስወደዉ በሚል ቃል ቢዘከር
 
ጅብ ነዉ የሚያክለዉ  አንድ  ሙሉ ሀገር
 
     //////////////////////////
           5/10/10
  
  16

ሰዉ መሆን ናፈቀኝ
 
 በዘር ማንዝር ጣጣ ምርጫየን ከማጣ
 
 በዘረኝነት ጦስ ዉስጤ ከሚቆጣ
 
 ከማልከፍለዉ እዳ ከማይሆን አራጣ
 
 ገብቸ ከምቀር ፊቴ ሳይገርጣ
 
 ሰዉ ሰዉ ልሽተትማ ሁሉንም በኩል ልይ
 
የእኔ ዘር ይበልጣል ብየ ከምታበይ
 
ክቡር ህሊናየን እንደያዝኩኝ ልቆይ
 
ስዉ መሆን ናፈቀኝ  እስኪ ሰዉ መስየ ልታይ
 
ልሻገርዉና ያን የዘረ ማንዝር ድልድይ
 
ልሂድ ከፍ ልበል በሰዉነቴ ላይ
 
             ///////////////////////
                  6/10/10
 
  17
 
ሀገር ምን ማለት ነዉ
 
 እየኖሩ መሞት በቁም ከመቀበር
 
 ስደትን ከማምለክ በነዋየ ፍቅር
 
መታገስ ይሻላይ ተቸግሮ መኖር  
 
በተሰጠን ጸጋ በአንዲት እናት ሀገር
 
 ለምንም ለማንም መቸም አንበገር
 
ሀገር እርስት ናት የልደት ስጦታ
 
ቅኝት ቋጠሮ ናት ቅኔ ማትፈታ 
 
ዘመን የማይሽርዉ የትዉልድ ቅብብል
 
 መድረኩ ሀገር ነዉ መቸም አይታበል
 
ስዉ ማለት ሀገር ነዉ ብለን ስንመሰል
 
አንድ እዉነት ይቀዳል
 
ሀገር ማለት ስዉ ነዉ የሚል ሀቅ ይወጣል
 
ይህ እዉነት ይመቻል
 
የሰዉን ክብር የሀገርንም ግርማ  ተሎ ያሳብቃል
 
ለአፍ ይጣፍጣል ለአንደበት ይሰላል
 
 የሀገር ሰዉ መሆን ለወሬ ይቀናል
 
        /////////////////////////
                  7/10/10  
 
  18
 
መንበርሽ መንበሬ 
 
 ምን ነካኝ አልኩና ተጸጸትኩ ከልቤ

ያለፈ ዉድቀቴን ጥፋቴን አስቤ

አንችን ማስከፋቱ ምንኛ ጥፋት ነዉ

መንበርሽ መንበሬ መሆኑን አዉቃለዉ

ያላች መኖሬን ስረግም እኖራለዉ

ልብሽ ዙፋን አለዉ ለእኔ የተሰራ

መንበሬ እንዴሆን አብሮ የተጠራ

እንቁ መልክት አለዉ የንግስና ማረግ

እንደገነት ተክል እንደማይጠወልግ

በመብራት በፋኑስ በሽ እንደሚፈለግ 

አንድ መልክት አለዉ ንግስት ነሽ የሚል

አንድ መልክት አለዉ ሙሽራ ነሽ የሚል

 የሰማይ ስባሪ መንበርን የሚክል

ስለዚህ ዉዴ ሆይ ከኔ አትራቂ

አብረሽኝ ሁኝና በመንብርሽ በኩል ክፋትን ሳታዉቂ

ስለፍቅራችን ወግ ትንሽ ተራቀቂ

ንግስቴ መሆንሽን በዛዉ አሳዉቂ

     /////////////////
      8/10/10
 
  19

መልክአ ሰባቱ ክዋክብት  


መንበር በህላዌ አክናፍ የስላልሽ

ስንት ጊዜ ሰገደ ለገጽ ለዉበትሽ

ሰባቱ ክዋክብት የአካላትሽ ጸዳል

ልዩ መሆንሽን በሀዝ ይናገራል

መልክአ _ ለአንገትሽ ብርሌ ሀመልማል

መልክአ _ ለአይኖችሽ ለሚያበሩ ሀያል

መልክአ_ ለከንፈርሽ በስስ ለሚያማልል

መልክአ _ ለዉብ ዳሌሽ ሰልፍ ለሚመስል

መልክአ _ ለወገብሽ እንደ ችቦ ቁጥር

መልክአ _ ለስንድር አፍጫሽ ከቀስት ለሚበደር

መልክአ _ ለዞማ ጸጉርሽ ከላይ ለሚወደር

ትጥቅ ነዉ አካልሽ እንደአንድ ወታደር

ስለዚህ ለነዚህ ስባቱ የአካላትሽ ማማ

ይያዝላቸዋል አርምሞ ጸሞና

አንችን ያየ ሁሉ በፍስሀ ገነት ይወለዳልና
    ////////////////
   26/10/10 

20

ይነገር የለም ወይ 
 
በወና በየብሱ ይነገር የለም ወይ

ፍቅርሽ ካገር ልቆ በግሀድ እንደሚታይ

 የተስወረዉም የካላትሽ ክፍል

ይነገር የለም ወይ አንዳች እንደሚክል

እንደስማይ ስባሪ ሊወድቅ እንደሚዋልል

የዳሌሽ ጠባብቁ ከየት ነዉ ሚከፋል

ይነገር የለም ወይ ከላይ እንደሚወርድ  

ቆንጃሽን አቋርጦ ወደ ባትሽ ሲወርድ
 
ይነገር የለም ወይ ባፈታሪክ ተረት

 የቁመናሽ መርዘም የቁመትሽ ልኬት

ይነገር የለም ወይ በእልፍኝ በአደባባይ

 የአንች ያለ ሁሉ በፍቅር እንደምጥይ

 ወይም በመዉደድ ቅስቶችሽ በጣር እንደምትግይ

 ይነገር የለም ወይ

                  ///////////////////
                    27/10/10
 
  21
 
ዶክተር አብይ ሀኪሜ ነህ  
  
  
በምድረ አሜሪካ በየሆስፒታሉ

በሀኪሞች ተረታ ምክር ሲያድሉ

ሞልቶ ከተረፈዉ ከሀኪም ጋጋታ

አንዳች የሆነልኝ ለእኔ የበረታ

ያዳነኝ  አልኖረም እንባየን የገታ

ሰባት አመት ሙሉ በዘረኝነት ጦስ

 ህሊናየ ደምቶ ዉስጤም ሲታመስ

አንድም አልተገኝም እንባየን የሚያብስ

በዘር መከፋፈል በብሄር ጥላቻ

አጥብቄ የራኩት  በብዙ ፍራቻ

ያንን የክፋት ዘመን ክፉን ዳርቻ

እግዚያብሄር አጠፋዉ በአንድ ብልጫ

 በይቅር ባይነት በአብይ አቅጣጫ

 መደመር ሆነልን የጤና የስላም

እንዲህ ነዉ ጀግና ሰዉ በሽተኛ ሚያክም

 እኔም ሆነ ሀገሬ ይህዉ ተፈወስን

አብይ የሆነ ሀኪም መሪ ስላገኘን

  ////////////////
     8/11/10
 
  22
 
ያላንች ክንዉን 


ስጠብቀዉ ዉየ ያሳደረኩት ተስፋ

 አንችን ስለመጣሽ ቆመ በወረፋ

የፍቅራችን ቅጡ ወጉ እንዳይጠፋ

የክፋት ሴራዉም ክፉዉ እንዳይፋፋ

በአንች ባለሽበት በሰላሙ መንገድ በተሎ ይለፋ

መስብሽ ድንቅ ነዉ ሀገር ያዳረሰ

ግረማሽም ግሩም ነዉ በሀገር የነገሰ

ቃልሽ ታማኝ እዉነት ክሯን ያልበጠሰ

ሀቅ የአንች አካል ዉብ እንደአንዲ አበባ

 እደፋሲካ በግ ለእርድ እንደሰባ

 እንደልጃገረድ እንደደመ ግቡ እንዳንዲት ወለባ

 ነገርሽ ክንዉን መዝረክረክ ያዉቅም

 አይንሽም አይሳሳም በሌላ አይቀናም

 ያላንች ተሳትፎ አዝመራዉ አይሽትም

 ያላንች ክንዉን አንድ ዘር አትወድቅም

 ያላንች ክንዉን ዳኛ ፍርድ አይፈርድም

 ያላንች ክንዉን ጸሀይ ማልዳ አትወጣም

 እንደዉ ያላንች ተሳትፎ ምንም ህግ አይጸድቅም

 ያላንች ክንዉን እኔ እንኳን ለግጥም ቅኔ አልቀኝም 

       //////////////
         11/11/10  

   23
     
ዉበቱ ይመስክር    
  
ልጅነት ጸጋ ነዉ ሀሰት የሌለበት

ያኔ የሆነዉን ምንም ሀቅ አትሳት

ለምን ትል እንደሆን ያችን እወቅባት

እዉነት አለችና በዚያ በልጅነት

 እኔም በዘመኔ እራሴን አወኩኝ

በአንዱ ጓደኛየ እራሴን አየሁኝ

ዉበቱ ነገርኝ በልጅነት ቋንቋ

በአካልም ባልደረጅ በአካልም ባልበቃ

ግጠም ያልኝን ልጅ አልፈራሁምና

በጉብዝና አወቀኝ ስሜም በዚያ ጸና

አልፋራሁምና ለትግል በቃሁኝ

ዉበቱ ልጅ ቢሆን ገንዘብ ባይሽልመኝ

አሁን ድረስ ያለ አክብሮቱን ሰጠኝ

               //////////////////
                28/11/10 
 
   24
 
አምልኮ መይሳዉ
 
 
የተነበር  መንበሩ የፍርዱ ዳኝነት
 
መይሳዉ ጥበብን ቃሉን ያሳየበት
 
በፍርድ ዙፋን ላይ በንጉሱ ግርማ  

ሹርባ የለበሰ ሁሉንም ያስማማ  

ከታቦር ከተማ ከዲቲ አላማ  

ከመይሳዉ ሌላ ማንም አይሰማ
 
መይሳዊያንም እኛ የሱ አምላኪ 
 
ያላድ ክንዉን ያላንድ ንክኪ
 
ለመሆን በቅተናል ታሪኩን ስባኪ
 
መይሳዊያን ይሉናል በስም የሚያቁነ
 
እኛ ከሰለጠን ቆየን ከነቃነ
 
አምልኮ መይሳዉ ዋና ስራችን ነዉ
 
ሹርባ በመሰራት ንጉሱን መስልነዉ
 
ጫት በመቃም ተግባር በምርቃና አወቅነዉ
 
በግጥም በስንኝ መዩን አደነቅነዉ ቴዲን አመለክነዉ 
      18/12/10
 
   25
 
የሰንበት ዉሎአችን 
 
 
እርሱአን የሚያስታዉስ የልቤን ትርታ 
  
ከዉስጤ እመቤት ጋር ለአፍታ መኝታ
 
እንደ ጀግና ሩምታ ማርኮ የሚረታ 
 
በአማኑዔል ግቢ በሀኪም ቆይታ
 
እንደአንድ ሰሞኑ ማበዴን ረስታ  
    
ተቀበኝ እንደዉ መመለሴን አይታ
 
እሁድ ወይ ቅዳሜ ይገስ  ዝምታ
 
      .....///..... 
      7/7/11 
 
  26

ለመቅደስ የተቀኘዉት ቅኔ
 
መቅደስ የእኔ  ሃይማኖት ሰላምና ገነት ብየ እንደተቀኘዉ
 ትላልቅ አይኖቹዋ እንደንጋት ኮከብ "ሰሜን" ሲያበሩ አየዉ
........................

    27
 
የጸጉርሽ ዛላዉ ዳር 

ርዝመቱ ዛላዉ እዳር የደረሰ
 
ከወገብሽ በታች በዝቶ የታመሰ
 
በዉበት ህላዌ ቁንጅና ያደሰ
 
በመወድስ ሀሩ ሰዉን አስታወሰ
 
በካፌ ቆይታ በዝናቡ ጠለል
 
ዉብ ፊትሽን አየዉት በጸጉሮችሽ መሀል
 
ከእናት ከወድምሽ ወሬ ተለይቶ
 
የጸጉርሽ ዉበቱ  ታየኝ ከሩቅ ጎልቶ
 
ከሙዚቃዉ ምት ጋር በፍቅር ተስማምቶ
 
         /////////////
         4/8/11 

  28
 
ሳገኝሸ ተለወጥኩ
                                                           
በጠፋዉ ዘመኔ ላስቀየምኩሽ ሁሉ
 
ተካክሶ መጣ ሳይጠፋ በሙሉ
 
እቱ የእኔ አካል ምን ብየ ልንገርሽ
 
ሳገኝሸ ተለወጥኩ አንድ ሚስጢር አለሽ
 
መቅዲ ናፍቂያለዉ ይቅርታሽ መልካም ነዉ
 
በነጋ በመሸ ሳስብሽ አድራለዉ
 
በራሴ ቁጭት ቃል እቃ ሰብሬአለዉ
 
ንዴቴን በልቁ ስወጣ ኑሬአለዉ
 
ያላንች በስተቀር ሀኪም አጥቻለዉ
 
ያላንች እንደማልኖር ያንን አዉቄአለዉ
 
 .........../////...........
      9/8/11
         
 
   29

በግራር ጥላ ስር
                                     
አቤት የእኔ ነገር አቤት የእኔ ፍቅር
 
የባይታዋር  ኑሮ  የባይታዋር አዳር
 
 በግራር ጥላ ስር ቃላት ስደረድር
 
እዳር በጎዳና የምዉል ስዘምር
 
በትንሽ ከተማ የምኖር በምስጢር
 
አቤት የእኔ ነገር አቤት የእኔ መላ
 
 ለህዝብ ለወገኔ ለሀገሬ ሳደላ
 
አንድ ምስኪን ፍጡር አንጀት  የምበላ
 
ተጠልየ አለሁኝ በግራሩዋ ጥላ
 
   ////////////////////
     12/8/11   
  
     30
 
በአዛዉንት መንኩሴና በአይነ ስዉር መሀል
         
ቢጫ ፋጣቸዉን ለብሰዉ በትካዜ
 
ፔስታል ዘርግተዉ ለልመና አባዜ
 
ከእኔ በስተግራ አዛዉንት መነኩሴ
 
ሲለምኑ አየዉ ሲሉ በስላሴ
 
ከወዲያ በሰተግራ አይነ-ስዉር ወጣት
 
የክብደት መለኪያ እዲመዘኑለት
 
ያቃጭላል በእጁ ምርኩዙ ባለበት
 
እኔ በመሀል ላይ ግጥም እጽፋለዉ
 
ምናብ እዲከፈት ሲጋራ አጨሳለዉ
 
ለምርቃናዉ ስልም ጫቴን እቅማለዉ
 
ከግራር ስር ሁኘም ቅኔ እቀኛለዉ
 
ከመንገድ ዳር ሁኘ ቀኔን  እገፋለዉ
 
        /////////////////////
           15/8/11


 31 
 

የወዳጀ መኖ                                                  



 ጠለፋ ይሉታል መኖ ምግብ ገላ

ከሰዉነት ጋራ አብሮ የሚደላ

ሊበሉት ሊጠጡት ሊያረጉት የሰላ

በአዋቂ  ተሰረቶ በዘዴ በመላ

 የቀረበ ማህድ የወዳጀ መኖ

 ሲቀርብ  አገኘዉት  በአንዴ  ተከዉኖ

ለስጋም ለነፍስም  አብሮ ተመጥኖ

እንደሸጋ ቆንጆ  አምሮት የሚያወጣ

የቅበላ ምግብ ጻርን የሚቀጣ

በአክስት በዘመዴ በወዳጀ መጣ

ከንግስና ድግስ ፍቅሩ የበረታ

እንደሰርግ ማህበር እንደጸበል ተርታ

 ብሉልኝ ጠጡልኝ የለገሰኝ ፌሽታ

ካለፈም በሃላም በማታ ፈረቃ

ለወግ ለተረትም ለትዝታም በቃ

         ////////////

        1/12/11
 
 32

በህይወት ህላዌ                       



ዘመን በነበረ በህይወት መነጠር

የእኔና የአንች እጣ ከስሩ የትነበር

በነጠላ ቃልሽ ወይም በትስስር

ይነገር ይወራ በዜማ በፍቅር

የይስሙላ መስሎ እንዳያደናግር

በህይወት ህላዌ ፍቅራች ይመስጠር

ሀዉልት ይሰራለት ይኑር በመዘክር

ዝናዉም ይወራ በሰፈር በመንደር

ነዉና ህላዌ  ፍቅር ሀያል ነገር

የእኔና አንች ዉሎ የማታችን አዳር

              ////////////

            24/11/11
 
 33

በዘፈቀደ ኑር

         
መኖር ከድማስ ወዲህ በራሰህ ክልል ላይ

መወድስ ችሎታህ ስጦታህ እዲታይ

በዘፈቀደ ኑር ከመስመር ወተህ ቆይ

አታቅድ አታስብ አንዲሁ በዘር ኑር

ያለጥንቃቄ ያለብሶት እድር

ታሽቶ ያልተበጠረ ትንታግ አንዳች ክምር

ድንገት ሀሴት ቢሆን ድንገት ቃል ቢፈጥር

በዚህም ቃል ድምር በዘፈቀደ  ዛር

አንዳች እምቅ ሀሴት በዉስጥህ ይኖራል

የታመቀዉ አንተ ነጻነት ይወጣል

               /////////////

               29/11/11

 34

አራዳ ነኝ ስትል


ዘመን ያለወጠዉ የእርድና መለኪያ

ብለህ የነገርከኝ እነዚያ መለያ

የንቃት ቋንቋዎች ስድብ ያነገቱ

ስንት ክብሮት ለአንተ አንቱታ አመረቱ

ምን ያህልስ ቆንጆ ድንግል ሴት እረቱ?

አራዳ ነኝ ካልከኝ ጋንግስተር ዱርየ በእንቅጩ በአይነቱ

ጀግና የመሆንህ የታለ እዉነቱ?

ከብልግና ሌላ የሌለዉ አንደበት

የራዳዉ ምኞትህ ተሞልቶ በዉሸት

 አራዳ ነኝ ስትል ነፍስህ አጣች እረፍት

 እኔም አንገት ደፋዉ ዋጠኝ አንዳች ሀፍረት

               ////////////////

                8/12/11

 35

በሙዚቃዉ ተርታ                    



 ህይወት በተስፋ ዝና በትዝታ ምቱ

እነጉራ ጌጡ ስንቱን አመረቱ

 ስንቱንስ በስክስታ ሸፍነዉ ዘመቱ

 በሙዚቃዉ ተርታ በስሜት ከወኑ

 እንዲሁ በምኞት ድነዉ ላያድኑ

 በቀድሞ  ጭዋታ  እያስተዛዘኑ

 በመጻፍ በመስማት ዘነጡ ዘመኑ

 የተሰጦ ዳና ስለተጎናጸፉ

 ከስዉ ተለይተዉ ቀንዝረዉ አረፉ

 ከያኒ የመሆን ይህ ነዉና ትርፉ

              ////////////

             30/11/11
 
 36 
 

ላይሽ እመጣለዉ                    


እነማን ነበሩ በህልፍ የወደዱሽ

ከጎበዙ መሀል በፍቅር አይን ያዩሽ

 እነማን ነበሩ በጥምቀት ያጀቡሽ

ሎሚ ተረከዝሽን ወርዉረዉ የመቱሽ

ወይስ የትኞቹ  ናቸዉ አብዝተዉ የሳሙሽ

በሰላምታ ሰበብ ሊያገኙሽ  ያሰቡሽ

እንግዲህ ህልቁ መሳፍርት የሰማዩ እይታ

ጨረቃ ብረሃን ክዋክብት በማታ

ይደምቁ ነበረ በአንች መምጣት ተረታ

ልቤም በቅኔ ቃል ለፍቅርሽ በረታ

ህሊናየም ነቃች መምጣትሽን ሰምታ

ሁሉም ጎበዝ ቆንጆ ህልቁ መሳፍርቱ

የዉበትሽን ዝና ሰምተዉ በተረቱ

ሊያዩሽ ይወዳሉ በአይን በብረቱ

እኔም እምጣለዉ ላይሽ በክረምቱ

ዶፉ ባያባራም ባትወጣም ጸሀይቱ

      /////////////////////

        27/11/11
 
37
 

ርካቦ ፍኖት                                                                                                                      


የተሰወረዉም ርካቦ ፍኖት

መገናኛ ድልድይ ከተሰየመለት

አንች ታች እኔ ላይ ሁነን ባለንበት

በጠንካራዉ አልጋ ሽዎች በተኙበት

የጨነገፈ ዘር ወድቆ ባልሞተበት

በዚያች አንዲት አዳር በዚያች አንዲት ስኬት

ከንፈርሽን ስሜ ጀግናን ባየዉበት

በዚያች አንዲት ምሽት በዚያች አንዲት ቅዕጽበት

በተሰወረ አዳር ርካቦ ፍኖት

እንደአንድ  ለናቱ  እንደቴዲ  አይነት

ቆፍጣና ወንዳወንድ በተረገዘበት

            //////////

           15/1/12

 38

አንች ሆየ ስልሸ


 አንች ሆየ ስልሸ ደስታ ይሰማኛል

ቅዳሴ ቁሜያለዉ ለዉበትሽ ፀዳል

ለመልክ ለቁመናሽ አቤቱ ይባላል

ዳኝነት ይቆማል ችሎት ይሰየማል

ለቁንጅናሽ ህብረት ፊደል ይመረጣል

እንደኔ ገጣሚ ስላንች ይቀኛለል

ፍሪዳ  ይጣላል ቁርጥ ስጋ ይበላል

በዉበትሽ ምክንያት በዉበትሽ ሀይል

ደሀና ሀብታሙ ባንድ ጣራ ስር እኩል ዉሎ ያድራል

እናም አንች ሆየ ስልሸ ደስታ ይሰማኛል

በልቤ መንበር ላይ በህቡ ነግሰሻል

አንች ሆየ ስልሸ ፍሰሀ ይሆናል

አንች ሆየ ስልሸ ጥሩ አየር ይነፍሳል

ኢትዮጵያየ ዉዴ ...  የሀገር ቅምጥል

የአንች ሆየ ሀሴት የትዉልድ  ሀመልማል

አንች ነሽ የግሌ ሱስ የራሴ አመል

    ///////////////////////
          27/6/12  

  
         39

የአንተን እዉነት አየዉ

              
መለከት ቢነፋ አርያም ቢወጣ

የበትረ ሙሴ ቃል ምንም ባትገረጣ

ፀጉሩን ያሳደገ ወይ አንድ መላጣ

የበቃ መነኩሴ  አንድ ቀን ቢመጣ

ከአንተ መይሳዉ ሹርባ አይታጣ

ያዉም ዉበት ያለዉ አምሮት የሚያወጣ

እናም ማንም እራሱን ቢያጸድቅ መሆን ቢያምረዉ ትልቅ

ያንተን ያህል እኮ ማንም አይራቀቅ

የአንተን እዉነት አየዉ በመቅደላ ስደቅ

በዚያ አሙሞትህ አንተ ስትታወቅ

በሽ ስትሞላ በሽ ስትደነቅ

ፍቅሬ መሆንህ ግን ብዙም አይታወቅ

                   ////////////// 
                     2/9/12 

 
        40 

ኪነ - መይሳዉ  


ጥበብ የት ተዘራች በአማራ መዲና

 ባህርዳር ያደገች የኪነት ህሊና

 በመደጉስ ብይን በጠልስም ክወና

 በመጣጥፍ ትይብ በመድረክ ትወና

 ያበቀለች ችግኝ የተስፋ ደመና

 የታክሲ የባጃጅ የመኪና ፍሰት

 ያገነናት ምስል የጶስተር ሙሽሪት

 የነፍጠኛ እስትፋስ የነፍጠኛ ኩራት

 በዚያች ከተማ ደምቃ ያየዋት

ቴዲ መይሳዉ ያች ያይን እራት

 ሙሉ በሙሉ ያንተ ፎቶ ናት

     ......  ///// ......

        5/13/12 

 

  .....  ተፈጸመ .... 
 

No comments:

Post a Comment