Wednesday, February 12, 2020

የከንፈርሽ ጸጋ

                                          


ትናንሽ ከንፈሮች የአንች ባይሆኑም

ለእኔ እንደተሰጡ ሀገሬዉ ባያዉቅም

አንችን በመሳሜ መዳኔን አልክድም

ባልሳም አረባም ባልሳም አልሰራም

ትንፋሽሽ ባይሞቀኝ ሽታሽ ባያሳሳኝ

አንዳች የእኔ የምለዉ ሰዉነት ባልኖረኝ

ያም ሁኖ ከናፍሮችሽን አጥብቄ እሻለዉ

ከመላ አካልሽ እነሱን ለመሳም እጅግ እወዳለዉ

የከናፍሮችሽ የተፈጥሮ ጸጋ

እንደጸጌረዳ እንደምተዋጋ

ጠዉልጋ እንደማታዉቅ በክረምት በበጋ

እንደምትጠበቅ መሽቶ እስከሚነጋ

ወይም እንደዉብ አበባ እንደምትፈነድቅ

እንደዉድ የአንገት ጌጥ ከአንገት እንደማይወልቅ

እንደንጉስ እልፍኝ በሽ እንደሚጠበቅ 

ከናፍሮችሽን እየሳምኩኝ ላድንቅ  

   /////////////////
      3/10/10

No comments:

Post a Comment